​የቀድሞ ሚስቱን በመግደል ወንጀል የተከሰሰዉ ግለሰብ በ21 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ::

በቂርቆስ ክፍል ከተማ ቀበሌ 08/09 ክልል ልዩ ቦታዉ ቡልጋሪያ ማዞሪያ መርሲ ሆቴል ተብሎ ከሚጠራዉ አካባቢ ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ/ም በህገ ወጥ መሳሪያ በመያዝ እና በመገልገል የሰዉ መግደል ወንጀል የፈጸመዉ ግለሰብ በጽኑ እስራት መቀጣቱን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ የአዲስ አበባ ማዕከል ማስተባበሪያ አስታወቀ::

ተከሳሽ ያየህ አዳሙ በ1996 ዓ/ም የወጣዉን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ ስር እና 809 ላይ የተደነገገዉን በመተላለፍ በፈፀመዉ ወንጀል በ2 ክስ መከሰሱን የዐቃቢ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል::ተከሳሽ ሰዉ ለመግደል  በማሰብ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንና ቦታ  በግምት ከጠዋቱ 12 ሰዓት ሲሆን የቀድሞ ሚስቱ ከነበረችዉ ሟች ገነት መኮንን ጋር በነበረዉ ፀብ መነሻነት ቂም በመያዙና እና ሟችን ለመግደል እንዲያመቸዉ አስቀድሞ ባዘጋጀዉ ኢኮልቲ 29 ሽጉጥ መጀመሪያ አንድ ጊዜ በመተኮስ የሟችን የቀኝ እጅ የሙሀል ጣት እና ትከሻዋ አካባቢ ከመታት በኃላ በድጋሜ መሳሪያዉን ወደ ጭንቅላቷ አስጠግቶ በመተኮስ የቀኝ ጭንቅላቷን በመምታት አንጎሏ ወደ ዉጭ እንዲወጣ እና ከፍተኛ ደም እንዲፈሳት በማድረግ ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኃላ ከቦታዉ ለማምለጥ ሲሞክር በአካባቢዎ ሰዎች የተያዘ በመሆኑ በፈፀመዉ የከባድ ሰዉ መግደል ወንጀል እና በ2ኛ ክስ ተከሳሽ ከሚመለከተዉ  ባለስልጣን ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖረዉ ከላይ በ1ኛ ክሰ ላይ በተገለፀዉ ጊዜ ቦታና ሁኔታ ወንጀል ለመፈፀም የተገለገለበትን ኢኮልቲ 29 ሽጉጥ ከሁለት ጥይት ጋር ይዞ የተገኘ በመሆኑ በፈፀመዉ የተከለከለ የጦር መሳሪያ መያዝ እና መገልገል ወንጀል ተከሷል::የፌዴራል አቃቢ ህገ ተከሳሹ በፈፀመዉ ወንጀል ተጠያቂ መሆን የሚችልበትን በፖሊስ የምርምራ መዝገብ መሰረት 6 የሰዉ ምስክሮች እና የሰነድ ማስረጃዎች እንዲሁም የሟችን አስከሬን የሚያሳይ ፎቶ ግራፍ በመያዝ በማስረጃነት አቅርቧል ተከሳሹ ተከላከል በተባለበት የግደያ ወንጀል ድርጊቱን ፈፅሜለሁ ጥፋተኛ ግን አይደለሁም ከሟች ጋር አብረን ስንኖር ሳለ ከእኔ ስትለይ ፀንሳ የነበረች ሲሆን አንተን ስለማልፈልግ ፀንሱን አቋርጨዋለሁ ስትላኝ ተናድጀ ደርጊቱን ፈፀሜለሁ በማለት የእምነት ክህደት ቃሉን የሰጠ ሲሆን በ2ኛ ክስ ድርጊቱን ፈፅሜለሁ ጥፋተኛ ነኝ ሲል አመኗል አቃቢ ህግ በበኩሉ በ1ኛ ክስ ምስክሮች ይሰሙልኝ ባለዉ መሰረት በማቅረብ ያሰማዉ ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹ በተከሰሰበት 2 የክስ ወንጀል ጥፋተኛ ብሎታል::የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርበ የተጠየቀዉ አቃቢ ህግ ተከሳሹ ወንጀሉን ድርጊቱን የፈፀመዉ ከቅርበ ዘመድ በላይ አምናዉ በአንድ ቤት ዉስጥ በትዳር ትኖር በነበረቸዉ ሟች ላይ በመሆኑ ተከሳሹን ሊያርም ሌሎቹን ሊያስተምር የሚችል በድንጋጌ የተቀመጠዉን መጨረሻ ቅጣተ እንዲወሰን ሲል ለችሎቱ አመልክቷል:: ተከሳሹም በበኩሉ የቤተስብ አስተዳዳሪ እና በአእምሮ መታወክ የተፈፀመ በስለሆነ ቅጣቱ እንዲቀልልኝ በማለት ጠይቋል::የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት መዝገቡን መርምሮ የወንጀል ድርጊቱ አፈፃፀም በጣም ጨካኝነተ አና ነዉረኝነት የሚያሳይ በመሆኑ ተከሳሽ የቀድሞ ባህሪዉ መልካም የነበረ ባለመሆኑ በማክበጃ በመያዝ የቤተሰብ እስተዳዳሪ መሆኑን 2 ማቀለያ በመቀበል ሃምሌ 29 /2008 አመት ምህረት በዋለዉ ችሎት በ1ኛ ክስ በ21 አመት ጽኑ እስራት አንዲቀጣ ሲወስን በ2ኛ ክስ የወንጀል ድርጊቱ አፈፃፀም ከፍተኛ ተብሎ በ100 ብር መቀጮ እና ሽጉጡ በእግዚቢት ለመንግስት ገቢ ይሁን በማለት ወስኗል::ዘገባውን ያጠናቀረው የፌደራል ጠቅላይ  ዐቃቤ  ህግ  የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

Advertisements

​Government offices now unable to sue each other 

The Council Of Ministers approved a 

Capital newspaper 

new civil code regulation manual that will change some of the legal trends in the country. 

The manual developed by the Federal Attorney General will be effective as of the current budget year. It will prohibit public institutions from getting into legal battles to solve disputes with each other.

Mulugeta Ayalew, deputy Attorney General, said that previously government offices would go to court to settle their disputes with other government offices. “With the new manual it will no longer be allowed,” he said.

The manual includes public enterprises. 

Government offices and public enterprises have to inform the government legal office when they seal any deal with an external body.

If government offices agree to a contract worth up to five million birr, they should inform and get a consultation from branches in the sub cities and Dire Dawa City Administration branch.

The Attorney General Head Office has to provide a consultation and be informed about the deal worth more than five million birr, according to the deputy Attorney General.

“If the public institution and public enterprises bypass the rule they will be responsible for any bad consequence,” he added

In the past trend public institutions and enterprises have faced problems in legal battles because there was no preconditions that forced them to get a consultation from the Attorney General, who replaced Ministry of Justice a few months ago.

“We have experienced that different government bodies approached the legal body for consultation when they faced problems,” he added. 

They come only when they have a problem, which has affected the interest of the government. When it observed they face a problem due to the deals or the contracts have  deficiencies. 

“But the new procedure helps the government bodies to make sound agreements in terms of the legal aspects,” he explained.

The Attorney General office has targeted to facilitate trainings for legal department officers at the government offices about the new manual.

The government legal body has also disclosed that it will establish branch offices in regional towns that will follow the interest of the federal government.

Under the new proclamation the Federal Attorney General is responsible for managing the legal issues that were managed by different offices like Ethiopian Revenue and Customs Authority and the Federal Ethics and Anti Corruption Commission.

By Muluken Yewondwossen

የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ 200 ዐቃቤያነ ሕግን ይፈልጋል

http://www.abyssinialaw.com/legal-jobs/item/1717-200 

በአዋጅ ቁጥር 943/2008 ዓ.ም የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተቋቋመ ሲሆን በረዳት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ከፍተኛ  ዐቃቤ ሕግ እና በዐቃቤ ሕግ ደረጃ 2 እና 1 200 የዐቃቤያነ ሕግ ክፍት የሥራ መደብ ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሠረት፡- 

ከማክሰኞ ነሐሴ 03/2008 ዓ/ም ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ማስረጃችሁን በመያዝ ፍትሕ ሚኒስቴር 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 302 በመቅረብ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ 

ለተጨማሪ ሊንኩን ይጫኑ

ለሌሎች ያካፍሉ

​ዳይሬክቶሬቱ በፍርድ አፈጻጸም የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን እንደሚታገል ገለፀ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የፍርድ ቤቱ የፍታብሄር ውሳኔዎችን በጥራትና በቅልጥፍና ተፈጻሚ ለማድረግ በውስጥና በውጭ የሚያንዣብቡ ኪራይ ሰብሳቢዎችንና ደላሎችን ከመቸውም ጊዜ በተሻለ እንደሚታገል ገለፀ፡፡
የፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ጉዳዩ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ታይቶ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ውሳኔ የተሰጠበትን የፍታብሄር ፍርድ በፍርዱ መሰረት ሳይፈፀም ሲቀር ፍርዱን እንዲያስፈፅም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ስር የተቋቋመ ዘርፍ ነው፡፡ 

ዳይሬክቶሬቱ ሐምሌ 24/2008 ስድስት ኪሎ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲሱ ህንፃው የ2008 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የበላይ አመራሮች፣ የዘርፍ ክፍል ሃላፊዎችና  ለተቋሙ ሰራተኞች ባቀረበበት ወቅት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ ውሳኔዎች በጥራት፣ በቅልጥፍናና በግልጽ አሰራር ተግባራዊ የሚሆንበት አገልግሎት ለመስጠት በውስጥና በውጭ ያሉ ኪራይ ሰብሳቢዎችን እና ደላሎችን ለመታገል ጠንክሮ እንደሚሰራ የከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛና የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ጎሽዬ ዳምጠው ገልፀዋል፡፡

በበጀት አመቱ በሰራተኞች የጋራ ትግል ከዚህ በፊት ችግር ይፈጥሩ የነበሩ ደላሎችን ከጥቅም ውጭ ለማድረግ  ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን  የገለጹት ዳይሬክተሩ ለመልካም አስተዳደር መስፈንና ፍርድ ያለ አድሎ በፍጥነት ለፍርድ ባለመብት ተፈጻሚ በማድረግ ሂደት የሰራተኞች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በዕለቱ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የዳይሬክቶሬቱ ሰራተኞች እውቅና የተሰጠ ሲሆን የተዘጋጀላቸውን የማትጊያ ሽልማትና የምስጋና ምስክር ወረቀት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ዳኜ መላኩ እጅ ተቀብለዋል፡፡

የፍርድ ባለእዳና የፍርድ ባለመብት የመጨረሻ የፍርድ መቋጫ የሚያገኙት ከፍርድ አፈፃጸም ዳይሬክቶሬት መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ አቶ ዳኜ ዳይሬክቶሬቱ ኪራይ ሰብሳቢዎችን እና ደላሎችን ለመታገል ለሚያድርገው ትግል የበላይ አመራሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞቹ እውቅና መስጠቱ ለሌሎች የተቋሙ የስራ ዘርፎች አርአያ የሚሆን ተግባር እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ክቡር አቶ ፀጋዬ አስማማው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ዳይሬክቶሬቱ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን  ለማረጋገጥ በሚያደረግው ጥረት  የሚያጋጥሙትን የግብአት እጥረቶች እና ከስራው ጋር የሚገናኙ የእውቀት እና የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለ1569 የፍርድ አፈፃፀም መዛግብት ዕልባት የሰጠ ሲሆን በዚህም ከ282 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለባለመብቶችና ለሚመለከታቸው አካላት ክፍያ ፈፅሟል፡፡

የተሻሻለው የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ ሆነ

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የተሻሻለውን የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅ ይፋ አደረገ።
የሚኒስቴሩ የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ዋሲሁን አባተ፥ ረቂቅ አዋጁ ከዚህ በፊት ከነበረው የተሻሻለ መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
ረቂቅ አዋጁ ተቀጣሪ ሰራተኞች አሁን እየከፈሉት ያለውን የገቢ ግብር መጠን እንዲቀንስ የሚያደርግና፥ የህብረተሰቡን ገቢ ከግምት ያስገባ የገቢ ግብር ምጣኔ፣ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ተብሎ የተቀመጠውን የደመዎዝ የግብር ጣሪያን የሚያሻሽልም ነው።
በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ መሰረት ደመዎዛቸው ከ6 መቶ ብር በታች የሆነ ተቀጣሪ ሰራተኞች ግብር አይከፍሉም።
ረቂቅ አዋጁ እንዲሻሻል የተደረገው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከደረሰበት ደረጃ አንፃር ዝቅተኛው ወርሃዊ ደመወዝ በማደጉ እና ከጊዜው እና የዜጎች ገቢ ጋር የተመጣጠነ የግብር ስርአት ለመዘርጋት መሆኑንም አስረድተዋል።
ሌላው በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ የተካተተው የግብር አይነት የንግድ ግብር ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ከግብር ነፃ የነበረውን 1 ሺህ 8 መቶ ብር ወደ 7 ሺህ አሳድጎታል።
በዚህ መሰረትም በዓመት 7 ሺህ ብር የኪራይ ገቢ ከግብር ነጻ በመሆን ከዛ በላይ ባለው ላይ ብቻ ግብር ይከፈልበታል።
አንድ ነጋዴ በተተመነበት ግብር ላይ ቅሬታ ቢኖረው፥ የፍሬ ግብሩን፣ መቀጮው እና ወለዱ ታሳቢ ተደርጎ የጠቅላላ ክፍያውን 50 በመቶ በማስያዝ ይግባኝ የሚልበት አሰራርም በረቂቅ አዋጁ ተቀይሯል።
ረቂቁ የግብር ይግባኝን የሚሰማ ራሱን የቻለ ተቋም እንዲቋቋምና የግብር ህግ የሚያዩ የተለያዩ ትርጎሞችን የሚያስቀር አሰራር እንዲፈጠርም ያስገድዳል።
በመጭው ሃሙስ እና ዓርብም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከንግዱ ማህበረሰብ፣ ከውጭ ሃገር ኩባንያዎች እና ከሙያ ማህበራት ጋር ውይይት ይደረግበታልም ነው ያሉት አቶ ዋሲሁን።
በውይይት ዳብሮ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ከቀረበ በኋላም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ፥ ከሃምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ፀድቆ ስራ ላይ እንዲውል እየተሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
በዚህም መሰረት ከመቀጠር በሚገኝ ገቢ ላይ ለሚጣለው ግብር ተፈጻሚ የሚሆኑትን ምጣኔዎች በሚከተለው መልኩ አስቀምጧል፤
income_tax_1.png
ሚኒስቴሩ ከዚህ ባለፈም በመኖሪያ ቤት እና በድርጅት ኪራይ የሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎችንም ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት በኪራይ በሚገኝ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑት ምጣኔዎችን በሚከተለው መልኩ አስቀምጧል፤
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ)