​ዳይሬክቶሬቱ በፍርድ አፈጻጸም የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን እንደሚታገል ገለፀ

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የፍርድ ቤቱ የፍታብሄር ውሳኔዎችን በጥራትና በቅልጥፍና ተፈጻሚ ለማድረግ በውስጥና በውጭ የሚያንዣብቡ ኪራይ ሰብሳቢዎችንና ደላሎችን ከመቸውም ጊዜ በተሻለ እንደሚታገል ገለፀ፡፡
የፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ጉዳዩ በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ታይቶ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ውሳኔ የተሰጠበትን የፍታብሄር ፍርድ በፍርዱ መሰረት ሳይፈፀም ሲቀር ፍርዱን እንዲያስፈፅም በፌደራል ጠቅላይ ፍርድቤት ስር የተቋቋመ ዘርፍ ነው፡፡ 

ዳይሬክቶሬቱ ሐምሌ 24/2008 ስድስት ኪሎ ያሬድ የሙዚቃ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው አዲሱ ህንፃው የ2008 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የበላይ አመራሮች፣ የዘርፍ ክፍል ሃላፊዎችና  ለተቋሙ ሰራተኞች ባቀረበበት ወቅት የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የመጨረሻ ውሳኔዎች በጥራት፣ በቅልጥፍናና በግልጽ አሰራር ተግባራዊ የሚሆንበት አገልግሎት ለመስጠት በውስጥና በውጭ ያሉ ኪራይ ሰብሳቢዎችን እና ደላሎችን ለመታገል ጠንክሮ እንደሚሰራ የከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛና የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ጎሽዬ ዳምጠው ገልፀዋል፡፡

በበጀት አመቱ በሰራተኞች የጋራ ትግል ከዚህ በፊት ችግር ይፈጥሩ የነበሩ ደላሎችን ከጥቅም ውጭ ለማድረግ  ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን  የገለጹት ዳይሬክተሩ ለመልካም አስተዳደር መስፈንና ፍርድ ያለ አድሎ በፍጥነት ለፍርድ ባለመብት ተፈጻሚ በማድረግ ሂደት የሰራተኞች የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

በዕለቱ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የዳይሬክቶሬቱ ሰራተኞች እውቅና የተሰጠ ሲሆን የተዘጋጀላቸውን የማትጊያ ሽልማትና የምስጋና ምስክር ወረቀት ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ክቡር አቶ ዳኜ መላኩ እጅ ተቀብለዋል፡፡

የፍርድ ባለእዳና የፍርድ ባለመብት የመጨረሻ የፍርድ መቋጫ የሚያገኙት ከፍርድ አፈፃጸም ዳይሬክቶሬት መሆኑን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ አቶ ዳኜ ዳይሬክቶሬቱ ኪራይ ሰብሳቢዎችን እና ደላሎችን ለመታገል ለሚያድርገው ትግል የበላይ አመራሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክቶሬቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ሰራተኞቹ እውቅና መስጠቱ ለሌሎች የተቋሙ የስራ ዘርፎች አርአያ የሚሆን ተግባር እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ክቡር አቶ ፀጋዬ አስማማው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ዳይሬክቶሬቱ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ተልዕኮውን  ለማረጋገጥ በሚያደረግው ጥረት  የሚያጋጥሙትን የግብአት እጥረቶች እና ከስራው ጋር የሚገናኙ የእውቀት እና የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለ1569 የፍርድ አፈፃፀም መዛግብት ዕልባት የሰጠ ሲሆን በዚህም ከ282 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለባለመብቶችና ለሚመለከታቸው አካላት ክፍያ ፈፅሟል፡፡

Advertisements

2 thoughts on “​ዳይሬክቶሬቱ በፍርድ አፈጻጸም የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን እንደሚታገል ገለፀ

 1. hi

  2016-08-04 19:27 GMT+03:00 Yared Gebrehanna :

  > ዳይሬክቶሬቱ
  > On Aug 1, 2016 4:39 PM, “YARED GEBREHANA LAW OFFICE” comment-reply@wordpress.com> wrote:
  >
  >> Yared Gebrehana law office posted: “የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የፍርድ
  >> ቤቱ የፍታብሄር ውሳኔዎችን በጥራትና በቅልጥፍና ተፈጻሚ ለማድረግ በውስጥና በውጭ የሚያንዣብቡ ኪራይ ሰብሳቢዎችንና
  >> ደላሎችን ከመቸውም ጊዜ በተሻለ እንደሚታገል ገለፀ፡፡ የፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ጉዳዩ በፌዴራል
  >> ፍርድ ቤቶች ታይቶ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ውሳኔ የተሰጠበትን የፍታብሄር ፍርድ በፍርዱ መሰረት ሳይፈፀም ሲቀር ፍርዱ”
  >>

  Like

 2. ዳይሬክቶሬቱ
  On Aug 1, 2016 4:39 PM, “YARED GEBREHANA LAW OFFICE” wrote:

  > Yared Gebrehana law office posted: “የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት የፍርድ
  > ቤቱ የፍታብሄር ውሳኔዎችን በጥራትና በቅልጥፍና ተፈጻሚ ለማድረግ በውስጥና በውጭ የሚያንዣብቡ ኪራይ ሰብሳቢዎችንና
  > ደላሎችን ከመቸውም ጊዜ በተሻለ እንደሚታገል ገለፀ፡፡ የፌደራል ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ጉዳዩ በፌዴራል
  > ፍርድ ቤቶች ታይቶ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ውሳኔ የተሰጠበትን የፍታብሄር ፍርድ በፍርዱ መሰረት ሳይፈፀም ሲቀር ፍርዱ”
  >

  Like

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s