ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዕጩ ዳኝነት መወዳደር ለሚፈልጉ አመልካቾች የወጣ ማስታወቂያ

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ አመልካቾችን አወዳድሮ እና አሰልጥኖ ለፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በዕጩ ዳኝነት መልምሎ ለሹመት ማቅረብ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች ከግንቦት 18/2008 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 /ሠባት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በመመዝገብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡

ተፈላጊ መስፈርቶች
በዳኝነት ለመስራት ፈቃደኛ የሆነ/የሆነች፣
ለህገመንግስቱ ታማኝ የሆነ/ የሆነች፣ ለህገመንግስቱ ታማኝ ስለመሆኑ/ ስለመሆኗ እና ህገመንግስቱን በሚቃረን ተግባር ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ/ተሳትፋ እንደማያውቅ/እንደማታውቅ የፅሁፍ ማረጋገጫ የሚሰጥ/ የምትሰጥ፣
ከዚህ ቀደም በጽኑ እስራት ተቀጥቶ/ ተቀጥታ እንደማያውቅ/እንደማታውቅ ማረጋገጫ የሚሰጥ/ የምትሰጥ፣
ጉባኤው በሚያደርገው ቃለመጠይቅ እና የማጣሪያ ፈተና አመርቂ ውጤት የሚያስመዘግብ/ የምታስመዘግብ እንዲሁም በሌሎች የባህሪ ምርመራዎች በእውቀቱ፣ በታታሪነቱ፣ በስነምግባሩ፣ በፍትሃዊነቱ እና በህግ አክባሪነቱ መልካም ስም ያለው ሆኖ የሚገኝ/ የምትገኝ፣
ዕውቅና ካለው ተቋም በህግ ትምህርት ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ ያላትና እና በከፍተኛ ነጥብ የተመረቀ/ የተመረቀች፣

ተፈላጊ የሥራ ልምድ፡-
• በህግ የመጀመሪያ ዲግሪ ላለው/ ላላት:- ቢያንስ 12 ዓመት በዳኝነት የሠራ/ የሰራች ወይም በሌላ ህግ ነክ ሙያ 14 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ ያላት፤
• በህግ የማስተርስ ዲግሪ ላለው /ላላት:- ቢያንስ 1ዐ ዓመት በዳኝነት የሠራ/ የሰራች ወይም በሌላ ህግ ነክ ሙያ 12 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ ያላት፤
• በህግ የዶክትሬት ዲግሪ ላለው/ላላት፡-  ቢያንስ 8 ዓመት በዳኝነት የሠራ/ የሰራች ወይም በሌላ ህግ ነክ ሙያ 1ዐ ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ ያላት፣
ዕድሜ ከ3ዐ ዓመት ያላነሠ፣
ዜግነት ኢትዮáያዊ የሆነ/ የሆነች፣
በጉባዔው ለሚወሠን ጊዜ እና ቦታ የቅድመ ዕጩነት ሥልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ/ የሆነች፣
የማመልከቻ ቦታ
• በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሚገኘው የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት
• የክልል አመልካቾች በስልክ ቁጥር 011 1 56 56 85 ላይ በመደወል በጊዜያዊነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ፡-
አመልካቾች የትምህርትና ሌሎች ማስረጃዎቻቸሁን ዋናውን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር አሟልታችሁ በአካል መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት በቅርብ ጊዜ የተዘጋጀ የስራ ልምድ እና

image

የስነምግባር ሁኔታችሁን የሚገልፅ ማስረጃ አያይዛችሁ መቅረብ አለባቸሁ፡፡

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባዔ ጽ/ቤት

Advertisements

ምላሽ ይስጡ

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s