12ኛ ዙር ኮንዶሚኒየም አሸናፊዎች ስቱዲዮ ዝርዝር ይመልከቱ።

አጠቃላይ-20-80-ቤት-ፕሮግራም-ስቱዲዮ-አሸናፊዎች-ዝርዝር

Advertisements

​ጄሶ ከጤፍ ዱቄት ጋር ቀላቅለዉ በመጋገር ለገበያ አቅርበዋል በሚል ክስ በተመሰረተባቸዉ ግለሰቦች ላይ ዐቃቤ ህግ ምስክሮችን አሰማ፡፡

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ታቦ

Federal Attorney General

ት ማደሪያ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ እንጀራ በመጋገርና በመሸጥ ስራ ላይ ተሰማርተዉ የነበሩ አልማዝ ሽፈሬ እና ጥሩሴት ወዳይ የተባሉ ግለሰቦች ከሰኔ ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ የጤፍ ዱቄትን ከጀሶ ጋር ቀላቅለዉ በማቡካት እንጀራ እየጋገሩ ለገበያ እያቀረቡ መሆኑን በአካባቢው ህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ ሐምሌ 11 ቀን 2008 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወቃል፡፡በመሆኑም ድርጊቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1ሀ እና 527/1ሀ እና ለ ስር የተመለከተዉን የሚተላለፍ በመሆኑ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ኮልፌ ቀራንዮ ፍትህ ጽፈት ቤት ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡በክስ መዝገቡ ላይ እንደተጠቀሰዉም ተከሳሾች ጄሶን ከጠፍ ዱቄት ጋር በመቀላቀል ለሰዉ ፍጆታ እንደማይበጅ በማድረግ በሰዉ ልጅ ላይ ከፍተኛ የክብደት መቀነስ እስከ ሞት ሊያደርስ በሚችል መልኩ እንጀራ አዘጋጅተዉ ለሽያጭ አቅርበዋል ይላል የፌዴራል ዐቃቤ ህግ ክስ፡፡ በመሆኑም በዋና ወንጀል አድራጊነት በፍፁም የሚጎዳ ወይም የተበላሸ እቃዎችና ምግቦችን መስራትና መሸጥ እንዲሁም ጥራታቸዉን ማርከስ ወንጀል ክሱ እንደተመሰረተባቸዉ የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያትታል፡፡ዐቃቤ ህግ የመሰረተውን የክስ መዝገብ አደራጅቶ መዝገቡን ለፍርድ ቤት ልኳል፡፡ ተከሳሾች የተከሰሱበትን ወንጀል እንዳልፈፀሙ የእምነት ክህደት ቃላቸዉን ለፍርድ ቤት ሰጥተዋል፡፡ ፍርድ ቤቱም እያንዳንዳቸዉ 80 ሺህ ብር ዋስትና አስይዘዉ የዐቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት በሰጠዉ ቀጠሮ መሰረት ትናንት ነሐሴ 11 ቀን 2008 ዓ.ም ምስክሮቹ ቀርበዉ የምስክርነት ቃላቸዉን ሰጥተዋል፡፡ በዐቃቤ ህግ መዝገብ ላይ እንደተገለፀዉም ምስክሮች ክሱን እንደ ክስ ዝርዝሩ በመመስከር አስረድተዋል፡፡ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ 2ኛ የወንጀል ችሎት ተከሳሾች ድርጊቱን እንደፈፀሙ በበቂ ሁኔታ የተመሰከረባቸዉ በመሆኑ በተከሰሱበት የህግ ድንጋጌ ተከላከሉ ብሏቸዋል፡፡የተከሳሾችን የመከላከያ ምስክር ለመስማትም ለጥቅምት 4 ቀን 2009 ዓ.ም ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በቀጣይም የፍርድ ውሳኔውን ተከታትለን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ዘገባው:-  የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ነው፡፡